ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
141

የሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በዞኑ አስተዳደር ሥር ላሉ መምሪያዎች አገልግሎት የሚዉል የእስቴሽነሪ ፣የኤሌክትሮኒክስ ፣የፈርኒቸር እና የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ነጥቦች እንደሚከተለው ተገልጸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሰሜን ጎጃም ገንዘብ መምሪያ ቢሮ  ቁጥር 08 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ /አገልግሎት/ ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት አምስት የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈረም አለበት፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ቢሮው ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ በመውረስ የራሱን አማራጭ ይወስዳል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ብር ለእስቴሽነሪ 40,000.00 /አርባ ሽህ ብር/ ፣ለኤሌክትሮኒክስ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ፤ለፈርኒቸር 60,000.00 /ስልሳ ሽህ ብር/ እና ለጽዳት እቃ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሽህ ብር/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን በ4፡30 የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ጨረታ በሚከፈትበት 16ኛው ቀን ክብረ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች ጨረታው ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምረያ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 11 መቀመጫዉን በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 ተባበሩት ማደያ ጀርባ የአማራ ህንጻ ዲዛይን ከተከራየዉ ቢሮ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የመጫረቻ ሰነዱ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ ዘግይቶ ለቢሮአችን ቢደርስ የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑት ድርጅቶች ሁሉንም ዕቃዎች /አገልግሎቶች/ በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽሎ በቀረበው በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የሰሜን ጎጃም ዞን  ገንዘብ መምሪያ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here