ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
124

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ዋና ጽ/ቤት ለፎ  ወ/ዓቃቢ ህግና ፎ/ወ አስተዳደር /ጽ/ቤት ማለትም ሎት 1 የቢሮና የአጥር ግንባታ ደረጃ 9 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭና በላይ እዲገነባላቸው ይፈልጋሉ፡፡ የግንባታ ቦታ ወረታ ዓቃቢ-ህግ ግቢና አስተዳደር ጽ/ቤት ነው፡፡ ሎት 2 ለሴ/መ ቤቶች እስቴሽነሪና ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅት

  1. በዘመኑ የታደሠ በዘርፋ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ካርድ ያላቸው፡፡
  2. የጨረታ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግንባታው 30 ተከታታይ ቀናት ለእስቴሽነሪና ኤሌክትሮኒክስ 15 ቀናት በፎ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /አንድ መቶ አምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆንና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላትና በደንብ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጽ/ቤታችን ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ለሎት 1 ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሽህ ብር/ ለሎት 2 ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሽህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግንባታ 30 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና 31ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ለእቃዎች 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. 16ኛውና 31ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  6. ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝርና ስፔስፊኬሽን ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ድርጅት ውል እንደያዘ ጨረታ ላላሸነፋት አካላት ተመላሽ ይሆናል፡፡
  8. አንድ ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተተንርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  9. አሸናፊው በውሉ መሠረት ከአላስረከበ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን መረዳት ይኖርበታል፡፡
  10. በጥቃቅንና አንስተኛ ተደራጅተው ለሚመጡ አካላት ካደራጃቸው ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራራሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አሰፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአሸናፊ ተጫራች የቀረበው በወድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ ሃያ በመቶ መቀነስ ወይም መጨመር የሚቻል መሆኑን፡፡
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 446 20 26 በመደወል ጠይቀው መረዳት ይችላሉ፡፡
  14. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፎገራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና /ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here