የደባርቅ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ አላቂና ቋሚ እቃዎች በሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 01 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣በሎት 2 ህትመት፣ ሎት 3 አላቂ የጽዳት እቃ ፣ሎት 4 ልዩ ልዩ መገልገያ ፤ በሎት 5 ቆሚ እቃዎች ግዥ ሲሆኑ እስከተቻለ ድረስ ውድድሩ በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከ10,000.00 /አስር ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ሁለት በመቶ ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ00 /ሃያ አምስት ብር/ በመክፈል በማዕከላዊ ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በደባርቅ ወርዳ ፍርድ ቤት ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ደባርቅ ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ጥራት የለለዉ እቃ ያቀረበ /ያመጣ/ ከሆነ በጥራት ኮሚቴዉ ተረጋግጦ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸዉ እዲሁም ጨረታዉን ካሸነፉ የዉል ማስከበርያ የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ዉስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም የጨረታ ማስከበረያዉ ከአንድ በመቶ ቢያንስ ከዉድድሩ ዉጭ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ ፅንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ማንኛዉም ተጫራች በነዚህ ቀናት ዉስጥ በማዕከላዊ ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት በግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀዉ ጨረታ ሳጥን ዉስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ሆኖ ይህ ቀን በበዓል /በካላንደር/ ቀን ከዋለ በሚቀጥለዉ የመንግስት የሥራ ቀን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከላዊ ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት በግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቀን 30/04 /2017 ዓ/ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ካለው በራሳቸው ፊርማ ፓራፍ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት /በድምር/ ዋጋ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛው ጠቅላላ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 117 08 30 /058 117 00 25 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደባርቅ ወረዳ ፍ/ቤት