በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ፍ/ቤት የግዥና/ፋ/ን//አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቡድን ለእናርጅ እናወጋ ወረዳ ፍርድ ቤት እና ለፈ/ብርሀን ን/ወ/ፍ/ቤት ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 ፈርኒቸር /የፋብሪካ ውጤ/፣ ሎት 5 ህትመት እና ሎት 6 አነስተኛ የእጅ መሳሪያ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ለሚገመቱ የጨረታ ሰነዶች የቫት ተመዝጋቢነት ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ግዥና/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቡድን ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ከጠቅላላ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት ብር ሁለት በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ-1 ገቢ አድርጎ የመሂ አንዱን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሲፒኦ ብሎ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን በማስፈር በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰነዱን ለማስገባት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ16 ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡ እለቱ የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡ አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 ተከታታየ ቀናት በኃላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት በመያዝ በአሸነፈበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ዋስትን በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጥ የባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ መቆያ ግዜን በተመለከተ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 40 ተከታታይ ቀን ውስጥ ጸንቶ ይቆያል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 59 63 39 /09 22 71 53 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው አቃውን ደብረ ወርቅ ከተማ ፍርድ ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ፍ/ቤት