ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
148

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለጉና በጌምድር ወረዳ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ሎት1. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎችና ስሜንቶ፣ ሎት2. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት3. የመኪና ጎማ እና ባትሪ፣ ሎት4. የስፖርት ትጥቅ እና ሎት5. የአዳራሽ ግንባታ ለማስገንባት የጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ7. እና ከዛ በለይ የሆነ ተቋራጭዎችን የእጅ ዋጋ ብቻ አወዳደሮ ማስገንባት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን ለምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግዡ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለመክፈላችሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/፤ ለሎት ሁለት 2,500.00 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለሎት ሦስት 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/፣ ለሎት አራት 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ እና ለሎት አምስት 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ  ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም  በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት  ወይም በጥሬ ገንዘብ  በመሂ-1 በማስቆረጥ በማስያዝ መረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ በጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ  ቀን ጀምሮ  ለተከታታይ 15 ቀን ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን  ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ 8፡30  ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. የዋጋ ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሚሞሉበት ሰዓት ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ መነካካት እና ሁለት አይነት ዋጋ ማስቀመጥ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ የማይመለስ  00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ ቀን ውስጥ ያሸነፉበት አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና  በጥሬ ገንዘብ  በመሂ-1 በማስቆረጥ በማስያዝ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርበው ውል መውሰድ ካልቻሉ በግዥ መመሪያው 1/2003  መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ ፡- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

የግንባታ እቃዎቹን ውል ከወሰደ ከ20 ቀን በፊት ውስጥ ማቅረብ የሚችል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 058 251 02 26 ደውለው አስፈላጊውን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here