ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

በምሥ/ጎጃም ዞን በክላስተር ደረጃ ለአራቱ ወረዳዎች ማለትም የጎ/ወ/ፍ/ቤት፤ የአዋባል ወ/ፍ/ቤት፤ የባሶሊበን ወ/ፍ/ቤት የአነደድ ወ/ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ለ2017 በጀት ዓመት ሎት 1 የጽፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኮምፒዉተር እና ተዛማች እቃዎቸ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 የህትመት ዉጤቶች፣ ሎት 5 ኤሌክትሪክና ተዛማች እቃዎችን፣ ሎት 6 የህንጻ መሳሪያዎች፣ ሎት 7 የዉጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 8 የአገር ዉስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 9 ፎቶ ኮፒ ማሽንና ኮፒዉተርና ተዛማች እቃዎች ጥገና እና ሎት 10 የአገር ዉስጥ ፈርኒቸር ጥገና የበር፤ የመስኮት የጠረጵዛ እና የሽልፍ ቁልፍ ጥገና ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በ2017 ዓ/ም በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኮምፒዉተርና ተዛማች እቃዎች ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በታችም ጠቅላላ ዋጋ ቢሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት አብሮ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳታፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ለሚገዙት እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 00 /ሃያ ብር/ በመክፈል ከሎት 1 እስከ ሎት 10 ድረስ ሰነዱን የ4ቱንም ወረዳ ፍ/ቤቶች ከጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ገንዘብ ያዥ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት አንድ በመቶ ከ1-10 ላሉት ሎቶች በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ቀናት 11፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ስዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጎ/ወ/ፍ/ቤት፣ የአዋበል ወ/ፍ/ቤት ፣የባሶሊበን ወ/ፍ/ቤት እና የአነደድ ወ/ፍ/ቤት የሁሎችም ወረዳዎች ለእያንዳንዱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች በተገኙበት ይታሸጋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የ4ቱም ወረዳዎች ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ጀምሮ የሚከፈት ሲሆን ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ፖስታው መከፈቱ የማይስተጓጎል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በሎት በጥቅል ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች መሆኑ ታውቆ የሁሉም እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም በዋጋ በመሙያዉ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ስም ፊርማ እና ማህተም መደረግ ይኖርበታል፡፡
  12. መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን ሃያ በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  13. አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ አስር በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /በሲፒኦ/ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት እቃውን በራሱ ትራንስፖርት ፤የአዋባል ወ/ፍ/ቤት የባሶሊበን ወ/ፍ/ቤት የአነደድ ወ/ፍ/ቤት ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ባሉበት ወረዳ አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጣው ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  17. የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  18. አሽናፊዉ ድርጅት በስማቸዉ የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለዉ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  19. ለበለጠ መረጃ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር የጎ/ወ/ፍ/ቤት 058 771 31 29 ብለው በውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የባሶ ሊበን ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here