ለደ/ጎን/ዞን ገንዘብ መምሪያ የቢሮ ግንባታ G+1 ለማስገነባት እና ለደ/ጎን/ዞን ትራንስፖርት ተ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የቢሮ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚቀርበው ፎቶ ኮፒ የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደርበት ጨረታ 140,000.00 /አንድ መቶ አራባ ሽህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያት ዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ግንባታ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ እትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመ 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 12 ከረዳት ገ/ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ 22 ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደ/ጎ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በ22ኛዉ ቀን በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ፣ እሁድና የህዝብ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ስለጨረታው ማስተካከያ ከፈለጉ ጨረታው ከመታሸጉ 15 ቀን ቀድሞ ማስተካከያ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- አሸናፊው በውሉ መሰረት በጥራት ሰርቶ በወቅቱ ካላስረበ በመ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ ወስዶ ውሉን በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት የዋጋ ድምር አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 07 53 በመደወል ማስረጃውን ማግኘት ይቻላል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ