በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ዋና ጽ/ቤት በስሙ ለተመዘገበው የመኖሪያ ቤትና ቦታ አድራሻ ደባርቅ ከተማ ቀበሌ 03 ልዮ ቦታው መድሃይኒያለም ሰፈር በእዳ ተረክቦ በስሙ ያስመዘገበውን ቤት በአዋሳኝ በምስራቅ ቢራራ ታደሰ፣ በምዕራብ አሀመድ አሊ፣ በደቡብ አስማማው ሃይሉ እና በሰሜን መንገድ የሚገኘውን ሁለት መቶ ሃምሳ ካሬ ሜትር ቤትና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተወዳዳሪዎች ሊያሟሉት የሚገባቸው፡-
- ማንኛውም ሰው የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ መወዳዳር ይችላል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለሚወዳዳሩበት የቤት ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) ከሁለት በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተወዳዳሪዎች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሲሞሎ ሥርዝ ድልዝ ካለው በራሳቸው ፊርማ ፓራፍ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ግለሰብ አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ስመ-ንብረት ዝውውር ማዛወር አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ያሸነፉበትን ገንዘብ ባይከፍሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረሱ ይሆናል፡፡ የስም ንብረት ዝውውርን /የቦታ ማዛወርያን/ በተመለከተ ሙሉ ወጭ በገዥ ወይም በአሸናፊ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ ዕትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ወይም ከ14/04/2017 እስከ 28/04/2017 ይሆናል፡፡
- ይሁን እንጅ የመክፈቻ የመጨረሻ 29 ቀን ቢሆንም ገና በዓል በካላንደር ዝግ በመሆኑ ምክንያት በ30/04/2017 ዓ.ም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩበት የቤትና ቦታ ጨረታ በቀን ከ20/4/2017 እስከ 25/04/2017 በጽ/ቤቱ በኩል መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ሚወዳዳሩበት የቤት እና የቦታ መነሻ ዋጋ 1,550,000 /አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ ሽህ ብር/ ሲሆን ከመነሻ ዋጋ በታች የሚሞላ ተወዳዳሪ ውድቅ ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሁነው የሚመረጡት ከተወዳዳሪዎች ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የሞሉት መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቻው ማግለል አይችሉም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ይሄን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታ ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በሥራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 11 ወይም 09 18 43 91 36 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደባርቅ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ዋና ጽ/ቤት