በአብክመ የሥራና ሥልጠና ቢሮ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 የሚገኘውን G+4 የቢሮ ህንፃ፣ሁለገብ አዳራሽ፣ የቢሮውን ምድረ ግቢ እንዲሁም የጥበቃ ቤቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የእድሳት ሥራ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ Gc-5/Bc-5 እና በላይ የሆኑ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመልካም ስራ አፈፃፀምና የቅድመ ብድር ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱ አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ስራና ስልጠና ቢሮ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 በግንባር በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ሥራው ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠናቆ ያስረክባል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ዋጋ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ጨረታው ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ 120 ቀን የሚቆይ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ስራና ስልጠና ቢሮ ቁጥር 001 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 10 በተገለፀው ቢሮ በ22ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ዘግተው 4፡30 ላይ ይከፈታል፤ በ22ኛው ቀን የበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22 ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታዉን ከመክፈት የሚያግደዉ ነገር የለም ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221800/0932095151 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
በአብክመ የሥራና ሥልጠና ቢሮ