የምዕራብ ጎንደር ዞን /ከፍ/ፍ/ቤት ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ በሥሩ ያሉትን 1. መተማ ወ/ፍ/ቤት 2. ምዕራብ አርማጭሆ ወ/ፍ/ቤት 3. አዳኝ አገር ጫቆ ወ/ፍ/ቤት 4. ቋራ/ወ/ፍ/ቤት አገልግሎት የሚሰጡ ሎት 1 ስቴሽነሪ ሎት 2 ቋሚ ዕቃ ሎካል፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 6 ህትመት እና ሎት 7 የመኪና እቃ በሎት ተዘርዝሮ ያቀረበ ሲሆን፡፡ የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 32 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምዕ/ጎ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ሂደት/ቢሮ ቁጥር 32 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ14/04/2017 ዓ/ም እስከ 28/04/2017 ዓ/ም ድረስ ከቀኑ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በቀን 28/04/2017 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ምዕ/ጎን/ዞን/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ሂደት በቀን 30/04/017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ውስጥ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 32 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ቢሮ ቁጥር 32 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 831 07 58 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ከተጫራቾች መካከል አሸናፊው ንብረቱን የሚያስረክበውና ውል የሚወስደው በምዕ/ጎ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን /ከፍ/ፍ/ቤት