በማዕከላዊ ጎንደር ዞን /ገ/ኢ/ት/መምሪያ የጠገዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የግንባታ እቃ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 ብትን ጨርቅ፣ ሎት 5 የተዘጋጁ አልባሳት፣ ሎት 6 የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 7 የውጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 8 የኤክልትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 9 የመኪና እቃ መለዋወጫ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተለውን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- እቃዎቹ በሙሉ ኦርጅናል እና አንደኛ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በጠ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት ደጋፊ የሥራ ሂደት በመቅረብ ከ21/04/2017 ዓ.ም እስከ 5/05/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በጠ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 5/05/2017 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጠ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በቀን 06/05/2017 ዓ.ም በ8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ የሚሆነው ከወረዳው ድረስ በመቅረብ ውል መውሰድ እና ንብረቱን ማቅረብ የሚችል፡፡
- ጨረታው የሚለየው በሎት በመሆኑ ዋጋውን ሲሞሉ ከፋፍለው መሙላት አይቻልም፡፡
- በሎት 4 እና 5 የተጠቀሰው የደንብ ልብስ ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ይሆናል፡፡
- በሎት 9 የተጠቀሰው የመኪና አቅርቦት እቃው የሚቀርበው የጥገና ጋራዥ በሚገኝበት ጎንደር ከተማ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጠ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 272 00 14 /09 53 24 40 07 በመደወለወ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጠገዴ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብት ጽ/ቤት