በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል/ት መምሪያ የደባይ ጥላን ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በመደበኛ በጀት ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የውሃ እቃ ፣ሎት 3 ስሚንቶ፣ ሎት 4 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 6 የዉጭ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ተጫራቾች
- ከላይ በተጠቀሱት ሥራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎችን ማያያዝ እንዲሁም የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙት እቃዎች የእቃውን ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ከደባይ ጥላት/ግን/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1 ብር 10,000 ፣ ሎት 2 ብር 10,000፣ ሎት 3 ብር 5,000፣ ሎት 4 ብር 2,000፣ ሎት 5 ብር 8,000 እና ሎት 6 ብር 1,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጥቅል /ሎት/ ስለሆነ ከተጠቀሱት እቃዎች ውስጥ አንዱንም ያልሞላ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን 11፡30 ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፓስታ በደ/ጥላ/ግ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፍል ለዚሁ ለተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን በሥራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 በ16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከሎት 1 እስከ ሎት 6 በ16ኛ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ጀምሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ጥ/ግን/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ16ኛው ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ጠቅላላ እቃዎች ከደባይ/ጥላት/ግ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሥር ባሉ ንብረት ክፍሎች ድረስ በመምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የአሸነፈውን ዋጋ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 058 257 02 57 /01 43/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ወይም ድርጅት ለመንገዱ የሚያስፈልጉ ማቴሪያል ወይም ቁሳቁስ ትራንስፓርት በተመለከተ ቦታው ድረስ ራሱ የሚያጓጉዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ ኢ/ል/ጽ/ቤት