በሰሜን ወሎ ዞን የወልድያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎች በመደበኛና በውስጥ ገቢ በጀት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሎት ምድብ 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ንዑስ ምድብ 1.1 ቋሚ የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ሎት ምድብ 2 የህንፃ መሳሪያ፣ እቃዎች ንዑስ ምድብ 2.1 የህንፃ መሳሪያ (የቴክኖሎጅ) እቃዎች ሎት ምድብ 3 የኤሌክትሪክ/ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት ምድብ 4 የጋርመንት ልብስና ክሮች፣ ሎት ምድብ 5 የግብርና እቃዎች፣ ሎት ምድብ፣ 6 አውቶ ሞቴቭ እቃዎች፣ ሎት ምድብ 7 ኮፒውተር እና ተዛማጅ ዕቃዎች እና ሎት ምድብ 8 የጽዳት እቃዎች ግዥ ይፈፅማል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ከላይ ከሎት ምድብ 1-8 ሎቶች እና ንዑስ ላሉት ምድብ በመስኩ የተሰማራችሁ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ሆኖ ማንኛውንም ወጭ በተጫራቹ በኩል የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ግምታቸው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ከዚህ በላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ውድድሩ በሎት በመሆኑ ተጫራቾች የእያንዳንዱን የዕቃ ዝርዝር ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የዋጋ ዝርዝር ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ21/04/17 እስከ 5/05/2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት ምድብ የጨረታ ሰነድ ብር00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከ21/04/2017 እስከ 5/05/2017 ዓ.ም ድረስ በግዥ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከ21/04/2017 እስከ 6/05/2017 ዓ.ም ድረስ በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ቀን በ6/05/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በተጨማሪም ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ተጫራቹ ናሙና ማቅረብ የሚገባቸው ካለ የሚያቀርብ ሆኖ ጥራቱ በባለሙያ እየተረጋገጠ ለምሳሌ የኮምፕተር ወርቀት እንዲሁም ሌሎች ማቴሪያሎች ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሁሉንም ዕቃዎች ኦርጅናል ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ለምሳሌ የፕሪንተር ቀለም እና ሌሎችም እቃዎች ኦርጅናል ብቻ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ሰነድ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ ውል ከመውሰድ በፊት ሃያ በመቶ በጀቱ እየተጣጣመ መጨመር ወይም መቀነስ የሚቻል ሲሆን በጀቱ እየታየ የሚሰርዝ ሎት ይኖራል፡፡ እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት በ10 ቀን ውስጥ እቃዎቹን ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ከሆነ በራሱ ወጭ ዕቃውን በማጓጓዝ ወልዲያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ሁኖ ንዑስም በየራሳቸው ንዑስ ድምር አሽናፊ ይለያል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 033 331 04 19 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወልድያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ