የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2017
የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብዓት አቅርቦት ቡድን ለ2017/2018 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በድምሩ 1,076,756 /አንድ ሚሊዮን ሰባ ስድስት ሽህ ሰባት መቶ ሃምሳ ስድስት/ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን በ 1 ዩኒየን በሥሩ ባሉ 144 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለመጓጓዘ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖረት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፡-
- የንግድ እና ገበያ ልማት ሚኒስቴር ቢሮ የታደሰ ንገድ ሥራ ፊቃድና የዘመኑ የመንግስት ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረበ ግዴታ አለባቸው፡፡
- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊከት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተሽከርካሪ ዝርዝር ተ.ቁ ፣የሴሌዳ ቁጥር ፣የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2017 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፊቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት ፣መጠን ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ መምሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሚወዳደሩበት ሁ/የገ/ህ/ስ/ ዳሞት ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በአብክመ ግብርና ቢሮ የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ በግብ/ግብ/አቅ/ገጠር ፋይናንሰ ቡድን ቢሮ 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማሰታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም 4፡00 ሰነዱን በሳጥኑ ዉስጥ በማስገባት የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተዉ በእለቱ በ4፡30 በመምሪያዉ በሚዘጋጅ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- መምሪያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መምሪያዉ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 08 71 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ