የአብክመ ሥራ አመሪር ኢንስቲትዬት ለ2017 በጀት ዓመት በግቢው ውስጥ ለሚሰጠው ስልጠና ለሰልጣኞች እና የሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት እቃዎች በአንድ ጊዜ ውል ተይዞ የሚቀርብ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኢንስቲትዬቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን/ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያ በጋዜጣ /ኦንላይን/ ከወጣበት ቀን ታህሳስ 21 /2017 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዬቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዬቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከታህሳስ 21/2017 እስከ ጥር 06/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጥር 06/2017 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ ጥር 06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በስራ አመራር ኢንስቲቲዬት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኢንስቲትዬቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በድምር /በጠቅላላ ዋጋ/ ነው፡፡
- ኢንስቲትዬቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ሥራ አመራር ኢንስቲትዬት