የላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2017 ዓ.ም በጀት አመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ምድብ 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ምድብ 2 የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ድርጅት መጫረት የሚችል መሆኑን እየገለፅን፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የሚያቀርቡት እቃ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳታፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙት እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለሥ00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ እና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለእቃዎቹ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በተለያዩ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይዘጋና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጐልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈውን እቃዎች በየፑሉ ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ዋጋ ነው፡፡
- በማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ከሎቱ ውስጥ ያንዱን እቃ ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ሥለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ቢሮ ቁጥር 4 ድረሰ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 13 99 /058 445 00 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
ላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት