በደቡብ ወሎ ዞን የወ/አምባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2016 በጀት አመት በመቀናጆ በጀት የውስጥ ለዉስጥ መንገድ ለማሰራት የማሽን ኪራይ ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ማሽኖች እስከ ዝርዝር መግለጫቸዉ ያሟሉና የተገለጹ ዝርዝር መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የማሽኖቹ አይነት ፡- 1ኛ. ዳምፕ ትራክ፣ 2ኛ. ሎደር፣ 3ኛ. ሞተር ግሬደር፣ 4ኛ. ቫይብሬተር /ሮለር/፣ 5ኛ. የውሃ ቦቲ እና 6ኛ. ዶዘር እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ማሽኖች ከ2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረቱ ማቅረብ የሚችል ስለዚህ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ ንግድ ፋቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላው በነፃ ገበያ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የማሽን የቴክኒክ ብልሽት፣ የስፔር ፓርት ለውጥ እንድሁም ዘይት ነክ ነገሮች እና የነዳጅ ወጭ ተጫራቹ በራሱ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የማሽን ኪራይ ስዓት የሚያዘው ለስራው ስራ ስዓት ብቻ ነው (የተፈጥሮ አደጋዎች ዝናብ እና ተያያዥ ችግሮች ከተከሰቱ የሚያባክነው ስዓት አይያዝም፡፡
- የማሽን መጓጓዣ እና መጫን ማውረጃ እንድሁም ከሚሰራበት ቦታ (ሳይት) ወደ ሌላ ሳይት መጓጓዣ መጫን ማውረጃ ተጫራቾች የሚችሉ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሹፌርና የኦፐሬተር እንዲሁም የረዳት አበል እና ሌሎች ወጭዎችን ተጫራቹ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የእቃው አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር ) በመክፈል በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ተዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመሂ 1 ማስያዝ ያለባቸው እና የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተፃፈለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውሥጥ መግባት ያለበት ሲሆን የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናል ፓስታ በጥንቃቄ በማሸግ በወይን አምባ ከተማ ማዘጋጃ አገልግሎት ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3፡30 ላይ ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የሚሰሩ ስራዎች ላይ ሃያ በመቶ የመጨመር ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ግዥ በጥቅል የሚፈጸም መሆኑን አውቆ ለእንዳንዱ ዝርዝር እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩት እቃዎች በሙሉ ጠቅላላ ለእያንዳንዳቸው ዋጋ ያለመሙላት ከጨረታው ውድቅ ያደርጋል ፡፡ እንድሁም አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ስራዎች ሙሉ በሙሉ ሰርቶ ካላስረከበ ክፍያ የማይፈፀም ይሆናል፡፡
- ለሥራው የሚያስፈልጉ የተለያዩ የሰርቪስ አገልግሎቶችን አሸናፊው ተጫራች የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0937909508 /0921526175 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- መንገዱ በደቡብ ወሎ ዞን በለገሂዳ ወረዳ በሆነችው በወ/አምባ ከተማ ውስጥ የሚሰራ ሲሆን ገረጋንቲ የሚመረትበት ቦታ ወይም ኳሪ ሳይት እስከ 5 ኪሎ ሜትር ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡