የአርባያ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ያገለገሉ 1ኛ.የውሃ ብረት ቱቦ 2ኛ.የውሃ ብረት ታንከር በዉስን ጨረታ አወዳድሮመሸጥይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚከተሉት መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( ቲን ) ያላቸዉ፡፡
- ለሚቀርቡት እቃዎች አይነት ዝርዝር በተመለከተ ( ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከ21/4/ 2017 እስከ 5 /5/ 2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ አርባያ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ማስገባትና መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች ለሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር መጠን ወይም የዕቃዉ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ በዋና ገ/ያዥ ገንዘቡን ገቢ አድርጎ ከሰነዱ ጋር ኮፒ አድርጎ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ 06/5/2017 ዓ.ም 3:30 ታሽጎ 4፡00 በአርባያ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዳቸዉን አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ፖስታዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ አርባያ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መጻፍ የለባቸዉም እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ፣ ስልክ ቁጥር አድራሻ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘና ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ጨረታው በክልሉ የከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ ማህበር ባወጣዉ የግዥ መመሪያ የሚተዳደር ይሆናል፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋችሁ የአርባያ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በግዥ ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት አስተዳደር ቢሮ ዉስጥ በስራ ስዓት በአካል ቀርበዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ወይም በስልክ ቁጥር 0582690283 (0963149833) (0920225488) ደዉለዉ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአርባያ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳ/ አገ/ ጽ/ቤት