ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
87

በሰሜን ጎንደር ዞን የዳባት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የህንፃ መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 5 የመኪና እና የጀኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 6 የፈርኒቸር እቃዎች እና ሎት 7 የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለካታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እና የሚሰሩ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዳባት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያየ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤታችን የስብሰባ አዳራሽ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ የሥራ ቀን ጠብቀን የምንከፍት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በየሎቱ በጥቅል ስለሆነ የሙሉ እቃ ዋጋ መሞላት አለበት ካልተሟላ ግን ከጨረታው ውጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት ዳባት ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና እቃዎችን ዳባት ሆስፒታል ባለው የንብረት መጋዝን በዝርዝር ማስረክብ የሚችል፡፡
  13. አሸናፊው እቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጅ ሥርዝ /ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  14. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ እቃ አቅርቦት ሃያ በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይቻላል፡፡
  16. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አስር በመቶ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  17. አሸናፊው ድርጅት መስሪያ ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 74 06 58 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ዳባት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here