ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
111

በምሥራቅ ጐጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ፍ/ቤት በ2017 ዓ/ም በጀት አመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 3 ህትመት ፣ሎት 4 የቢሮ እቃዎች/ፈርኒቸር/ ፣ሎት 5 አነስተኛ የቢሮ እቃዎች እና ሎት 6 የጽዳት እቃዎች በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘመነ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘውትር በሥራ ስዓት እነ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ንብ/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 የማይመለስ00 (ሃምሳ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሃ 1 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ (ስፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ወይም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ይታሸግና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት  አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ ፣እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ስዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ስዓት ይከፈታል፡፡
  7. በጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆኑ ነገሮች መኖር የለበትም፡፡ በጨረታ ሰነዱ እና በፖስተው ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
  8. በለሙያ የሚያረጋግጡ እቃዎችን በባለሙያ እያረጋገጥን የምንረከብ መሆኑና አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸው እቃዎችን በእነ/ወ/ፍ/ቤት ሥር ባለው ንብረት ክፍል ድረስ አስፈላጊውን ወጪ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  9. በእያንዳንዱ ሎት መ/ቤቱ አሸናፊ የሚለየው ጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች በየ ምድቡ የቀረቡትን ሙሉ በመሉ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡
  10. ከሎት 1-6 ላሉ የሎት ምድቦች ጽ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሳይቀየር ሥራው ከጠቅላላ መጠን ላይ ሃያ በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀን ይችላል፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 01 46 ደውሉ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የእነማይ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here