ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
91

የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቡድን በተያዘው ለ2017 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የኤሌክትሪክ ሲቲ እቃዎች ፣ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3. የኮንስትራክሽን እቃዎች ፣ሎት 4. የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 5. የአውቶሞቲቭ እቃዎች ፣ሎት 6. የደንብ ልብስ እቃዎች ፣ሎት 7. የልብስ ስፌት እቃዎች እና ሎት 8. የግብርና እቃዎችን በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

  1. ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩት የግዥ ዋጋ /ጠቅላላ ዋጋ/ ሁለት በመቶ በባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡15 ታሽጎ በዚያው እለት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ከዚህ ሰነድ ባልተጠቀሱ ነገሮች በግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊ የምንለየው በሎት በተሞላው ጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያሸነፉትን እቃ ከዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተመሳሳይ እና ጥራት የሌለው እቃ ማቅረብ በህግ ያስቀጣል፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮሌጁ ግ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 223 04 12 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here