ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
97

የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል ሎት 1 ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ እና እና ሎት 4 የተሸከርካሪ ጎማ ግዥ አገልግሎት የሚሆን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይጋብዛል፡፡

  1. ቲን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉና ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ግዥ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ መሆኑ ሲገመት /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5,000.00 (አምስት ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ መሸጫ ዋጋ00 (አራት መቶ ብር) ነው፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱ ከ28/04/2017 ዓ.ም እስከ 12/05/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
  5. ጨረታዉ የሚከፈተዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ13/05/2017 ዓ.ም በ5፡00 ታሽጉ 5፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  6. ማንኛዉም ተጫራች /ተወዳደሪ/ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት በ5 ቀን ዉስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ዉል መያዝ አለበት፡፡
  7. የንግድ ፈቃዳቸው ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር ተዛማጅ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል ቢሮ ቁጥር 10 በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 01 45 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  9. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here