የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ህትመት ፣ኤሌክትሮኒክስ ፣ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ ፈርኒቸር እና የደንብ ልብስ እነዚህን በዝርዝር የተጠቀሱትን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስስሆነም፡- ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴትታክስ ቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ በሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ሙሉ አድራሻ፤ ስልክ ቁጥር በማስፈር ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ዋጋቸውን ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተመሰከረስት /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የዋጋውን ሁለት በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫረቾች ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ28/04/2017 ዓ.ም እስከ 18/05/2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከጃዊ የመጀ/ደ/ሆ/ግ/ፋይ/ንብ/ስ/ደ/የሥራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ 00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 19/05/2017 ዓ.ም በ3፡00 ታሽጎ በ3:30 ይከፈታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝሩን /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል፡፡
- እቃውን ጃ/የመ/ደ/ሆ/ መጋዘን ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተቋሙ ጨረታውን ከጠቅላላ ድምሩ ሃያ በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 278 03 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል