ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

በባ/ዳርና አካ/ከፍ/ፍ/ቤት የደቡብ አቸፈር ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤታችን የሚያስፈልጉ አመታዊ ግዥ ማለትም ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. ህትመት ፣ ሎት3. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት4. የእጅ መሳሪያ ፣ሎት5. ቀሚ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድር  መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ /ብርእና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ሠዓት በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር00/ሃያ ብር/ በመክፈል ደ/አቸ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢ/ቁ 11 መግዛት ይቻላል፡፡
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ(ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁስት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በየምድቡ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ በደ/አቸ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ክፍለል ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፡፡
  9. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን በስራ ስዓት ከጠዋቱ በ2:30 ታሽጎ በ3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥስው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት 10% የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉሰድ አለበት፡፡ እንደዉሉ ባይፈፀም ግን የጨረታ ማስከበሪያዉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት  ይኖርባቸዋል፡፡ በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው እቃዎች ስአንድም እቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  12. መ/ቤቱ በጨረታ ከሚገዛው ዕቃ መጠን እስከ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  13. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማስጫኛና ማውረጃ እንዲሁም ትራንስፖርት ወጭውን ችሎ ደ/አቸ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  14. መ//ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፤የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም ስርዝ ድልዝ ከሆነ ፓራፍ መደረግ ይኖርበታል፡፡
  15. አሸናፊ የሆነው ድርጅት ለሰነድ ምርምራ አገልግሎት ክፍያ ራሱ የሚከፍል ይሆናል፡፡
  16. በጨረታ ማስታወቂያው ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 223 01 60 በመደወል ቢሮ ቁጥር 11 በአካል በመምጣት መጠቅ ይችላሉ፡፡

 ደቡብ አቸፈር ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here