ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
144

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማች ዕቃዎች፣  ሎት 2. የጽሕፈት መሣሪያዎች፣  ሎት 3. ፈርኒቸር፣ ሎት 4. ሕትመት እና ሎት 5. የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 56 ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በቢሮው ቢሮ ቁጥር 50 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ሰኔ 04/ 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም  ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 50 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 50 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 82 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here