ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

ቁጥር አካ/ደ/ጥ/ል/ባ ግ/03/2ዐ17

በአብክመ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን እና የጣና ሀይቅና ሌሎች ውሀማ አካላት ጥበቃ እና ልማት ኤጀንሲ በመደበኛ በጀት ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ እስቴሽነሪ ፣ፈርኒቸር እና የጽዳት እቃዎችን  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ  ከፋይ የሆኑ  አቅራቢዎችን በዚህ ግልጽ ጨረታ እንድትወዳደሩ   ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ  ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታውን ሠነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት                                                                                                        ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር ጋንቢ ቲችንግ ሆስፒታል ጎን ካለው በመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር  ዳይሬክቶሬት ፤ገንዘብ ያዥ  ቢሮ ቁጥር 10 ፤60∙00 /ስልሳ ብር / የማይመለስ በመክፈል መግዛት  ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የጨረታው ሠነድ በሚጠይቀው መሠረት ሞልተው በታሸገ ፖስታ በማድረግ በ16ኛው ቀን አስከ 3፡00  ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 14 አጠገብ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲገባ መደረግ አለበት፤ ጨረታው በእለቱ  3፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ባይገኙም  ከመክፈት አያግድም፡፡
  4. ተጫራቾች ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ በባንክ ወይም በኢትዩዽያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ማቅረብ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ አብረው ማቅረብ አለባቸው የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  5. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. ከ 20 ሺህ ብር በላይ ለሆኑ ግዥዎች የቫቱን 50በመቶ ቢሮው የሚያስቀር መሆኑን ይገልጻል፡፡
  7. ከብር 200 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  8. ቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ስም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው ሊሆን ይገባል፡፡
  9. ተጫራቾች ዋናውን እና ኮፒ የመጫረቻ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ሌሎች በጨረታ ሰነዱ ያልተገለጹ ጉዳዮች በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-62-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

በአብክመ አካ/ደ/ጥ/ል/ባ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here