ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
123

በማዕ/ጎን/ዞን የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለነጭ/ወ/አጠቃላይ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽፈት መሳሪያ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃ ፣ሎት 3 ፈርኒቸር ፣ሎት 4 ኤሌክትሮኔክስ ፣ሎት 5 የመኪና ቋሚ እቃ ፣6 የመኪና አላቂ ዕቃ ፣ሎት 7 የመኪና ጎማ ፣ሎት 8 የጣውላ ቤት ሥራዎች ከሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
  3. ግዥው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. በፍትህ ውል መውሰድ የሚችሉ፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያለቅድምያ ክፍያ የሚያቀርብ መሆኑን ከወዲሁ ማወቅ አለበት፡፡
  6. ጨረታው ላይ ለሚሳተፉ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን ህጋዊ ዶክመንት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ በተ.ቁ 1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ እና ኦርጅናሉን ለየብቻ በማሸግ ሁለቱንም ፖስታዎች በጥንቃቄ በአንድ ፖስታ በማሸግ በሳጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የሎት ሰነድ00 (ሀምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ረዳት ገያዥ ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሃ/1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለእቃ ግዥዎች 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና በ16ተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ክፍት ሁኖ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ፖስታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ዋጋ ሳይሞላ ቢቀር ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በማስያዝ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሃ/1 በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ሳምፕል ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በማየት የጨረታ ሰነዱን መሙላት አለባቸው፡፡
  14. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. መ/ቤቱ በሚገዛው ዕቃ ላይ ሃያ በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብት አለው፡፡
  17. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ነው፡፡
  18. አሸናፋው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ በነ/ጭ/ወ/ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ማስረከብ አለባቸው፡፡
  19. ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 333 03 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ነባሩ ጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here