ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

በደቡብ ወሎ ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ የወረኢሉ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት 2 የኤሌክትሪካል ኤለክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ሎት 3 የህንፃ መሳሪያዎች ፣ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች ሎት 5 የሆቴል ቱሪዝም ማዕሰጠኛዎችን  ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም:-

  1. ተጫራቾች በከተሰማረበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደስ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በታች ከሆነ በድርጅቱ በስማቸው የታተመ ሁለት በመቶ ደረሰኝ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  2. ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ00 (ሃምሳ ብር) በአንድ ሎት በመክፈል ከኮሌጁ ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጠቅላላ ዋጋ ድምር ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በስም በታሸገ ኢንቨሎኘ ሙሉ አድራሻውን በመጥቀስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላበት ቦታ ካለ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታው ማሸጊና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ:- ተጫራቾች መ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት የተጠየቁትን ዕቃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በወረኢሉ ፖሊ/ቴክ/ኮሌጅ በግንባር በማቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 116 02 50 /033 116 04 85 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወረኢሱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here