ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት አመት አላቂ የቢሮ እቃዎችን /እስሽቴሽነሪ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ  ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያቁ /ቲን/ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የግበር ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የግዥዉ መጠን 200,000/.00 ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን  የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒ  ከጨረታ  ሰነዱ ጋር አያይዘው  ማቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር  መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/  እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር  ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን  ቢሮ  3  የማይመለስ00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ  ምክንያት  በሚመለከታቸው የመንግስት  ተቋማት  ያልታገዱ  መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረዎዉ በዋጋ መሙያዉ ቅፅ ላይ ማንኛውንም   የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ  የጨረታ ሰነዱ  በፖስታ ታሽጎ   የድርጅቱ ክብ  ማህተም ፣ፊርማ ፣ስም እና አድራሻ  በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ  የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ  ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / የሚሞሉትን ጠቅላላ ድምር ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ  የክፍያ ትዕዛዝ  /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም በሆስፒታሉ ገቢ ደረሰኝ መሂ-1   ገቢ በማድረግ ዋናዉን ደረሰኝ  ከፖስታው ውስጥ  አብሮ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ የዉል ማስከበሪያ  ዋስትና  ማስያዝ  አለባቸዉ፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ  ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት  በ8፡30  ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት  ሆኖ ባይገኙ  ግን ፕሮግራሙ  የማይስተጓጎል  ይሆናል፡፡
  11. ሆስፒታሉ አሸናፊዉን በሎት /በጠቅላላ ድምር/  የሚያወዳድር   ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች እቃዉን በራሳቸዉ ወጪ በተጠየቀዉ ስፔሰፊኬሽን መሰረት እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በማምጣት ገቢ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here