ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

በደ/ጎንደር ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግን/አስ ቡድን ለ2017 በጀት አመት ለመንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የዶዘር ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ሙሉ አድራሻቸውን በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም መምታት አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውላል፡፡
  10. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉሉ አይሆኑም ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሃደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  11. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  13. በማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 28 07 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሰሙጃ ወረዳ ገንዘብና ኮነሚ //ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here