በደ/ጎንደር ዞን አ/ዘመን ከተማ የሚገኘው ርብ ኃላ/የተወሠነ የኅብረት ስራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ቀበሌ 04 በመደበኛ በጀት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ባለቢዝመንት ሦስተኛ ፎቅ (B+G+3 ፎቅ) ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለብረት አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ በመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችል በመሆኑን ይጋብዛል፡፡
- አቅራቢዎች ህጋዊና በዘመኑ የታደሠ የንግድ /የሥራ/ ፈቃድ እንዲሁም ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የወጣው ጨረታ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ እንደሚሆን ሲገመት የተጨማሪም የእሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ በአማረኛ ቋንቋ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚሞሉበት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፣ፊርማቸው እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖረባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በአ/ዘመን ከተማ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ለሃያ አምስት ተከታታይ ቀናት የመጫረቻ ሠነዱን ዋናው ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በአካል /ህጋዊ ወኪላቸው በኩል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ መዝጊያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- የብረት አይነት ፣ብዛትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ለ25 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ በ26 ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ደረስ ማስገባትና በ4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት/ ባይገኙም/ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ሰነዱ በአንድ በጥንቃቂ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦሪጅናል ሰነዶ ፖስታ ውሥጥ በማደረግ መቅረብ አለባቸው፡፡
- ዩኒዬኑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የብረት አቀራረብ ሁኔታ በተመለከተ ተጫራቾች መመሪያ ይመልከቱ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 444 00 61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ርብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ስራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን