ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
105

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአይከል ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፈ/ን አስ/ድን በከተማው የውስጥ ገቢ እና በክልሉ በጀት የአይ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ ጽ/ቤት ለሚያሰራው መሠረተ ልማት ሥራ ማለትም ሎት 1  የጠጠር መንገድ Package/NoAYKELE MAIN/1/24/25 ከአለምቀን ሸድ እስከ አባይ ሲሳይ ቤት 240 ሜትር ሎት 1 የኮብልስቶን መንገድ ጥገና Package/No AYMEL/C/MAN/01/24/25 499.82 ካ.ሜ  ሎት 1 የውሃ መስመር ጥገና 75 ሜትር Package/No AYMEL/C/MAN/01/24/25 የግንባታ ሥራዎችን ከደረጃ 7 እስከ ደረጃ 1 ያሉት ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ለግንባታ ሥራዎች ለአገልግሎት ግዥዎች ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የምንፈልገውን የሥራ እና የዕቃ ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው መ/ቤት ወቅታዊ የሆነ እና ለጽ/ቤቱ በአድራሻ የተጻፈ ማስረጃ በማቅረብ በነጻ ከአይከል ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 29 የጨረታ ሰነዱን መግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ሎት 1 የጠጠር መንገድ 28,297.00 (ሃያ ስምንት ሽህ ሁለት መቶ ዘጠና ሰባት ሽህ ብር) ሎት 2 የኮብልስቶን መንገድ ጥገና 30,574 (ሰላሳ ሽህ አምስት መቶ ሰባ አራት ብር) ሎት 1 የውሃ መስመር ጥገና ብር 5,453 /አምስት ሽህ አራት መቶ ሃምሳ ሦስት ብር/ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ እና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም በጥቃቅን የተደራጁ ከሆኑ በጨረታ ለመወዳደር የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን ወቅታዊ የሆነ እና ለጽ/ቤቱ በአድራሻ ከአደራጃቸው መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን እና ሠነዱን አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ 2 ቅጅዎች ዋና እና የቅጅ በማለት በጥንቃቄ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን 05/05/2017 ዓ.ም እስክ 25/05/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ አዓት 2፡30-6፡30 እና 7፡30-11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በአየር ላይ ይውላል በ22ኛ ቀን ማለትም 26/05/2017 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ደግሞ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አ/ከ/አስ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 11 54 ወይም 058 333 1148 ደውለው ማረጋገጥ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- የድርጅትዎ ማህተም በየገፁ ማድረግዎን አይዘንጉ፡፡ ጨረታውን  የምንለየው በጥቅል ዋጋው መሆኑን አውቀው በጥንቃቄ እንዲሞሉ እንዲሁም የሚቀርቡ ማስረጃዎች በእያዳንዱ ገጽ ኮፒ በማድረግ እንዲያስይዙ እና ጨረታውን ሲሞሉ የተቋማችን አድራሻ መግለጽ እና ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ አለመኖሩን ያረጋግጡ

የአይከል ከተማ አስተዳደር  ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here