ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

በአብክመ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ለኮሚሽኑ አገልግሎት የሚዉል የህትመት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች  የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት ያላቸው፣
  4. የሚገዙ ዕቃዎች ዋጋ ከ200 ሽህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማያያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 እስከ 4 የተገለጹትን መስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያየዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የህትመቶችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚገዙት የህትመት አገልግሎቶች የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  12. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ስዓት ተዘግቶ 4፡30 ስዓት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 0582180014/ 0582181103 ይደውሉ፡፡

አ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here