በምስራቅ ጐጃም ዞን የሰዴ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለሰዴ ወረዳ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽቤት አገልግሎት የሚውል ድልድይ በግልፅ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛሉ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ተቋራጮች የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው
ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች G+5 እና በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የግንባታውን 10 በመቶ ስራ በወረዳው ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል ከሰዴ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ከረዳት ገ/ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጭራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ሚወዳደሩበት ዓይነት ጨረታ 180,000 /አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያዘው ገንዘብ በሰዴ ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ገቢ ተደርጎ ከፋይናንሽያል ዶክመንቱ ጋር ገቢ መደረግ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ሃሳቡን ማለትም የፋይናንሽል ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰዴ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት እና እስከ 31ኛው ቀን እስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይቻላል ። ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት አለባቸው። በመሆኑም ኮፒ ባለማስገባቱ ከውድድር ውጭ ሊያስደርግ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 02 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ በ31 ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ሙብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት ፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ አልያም በስልክ ቁጥር 0585554173 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡
የሰዴ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት