ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
92

በምሥራቅ ጐጃም ዞን የሰዴ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ለሰዴ ወረዳ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ድልድይ በግልጽ ጨረታ  ማስራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛሉ፡፡

  1. በዘርፍ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ፣የተቋራጮች የበቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች G+5 እና በላይ የሆኑ፡፡
  6. የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. አሸናፊው ተጫራች የግንባታውን አስር በመቶ ሥራ በወረዳው ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከሰዴ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ከረዳት ገ/ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ዓይነት ጨረታ 180,000.00 /አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጥሬ ገንዘብ የሚያዘው ገንዘብ በሰዴ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ገቢ ተደርጎ ኦርጅናሉን ከፋይናንሺያል ዶክመቱ ጋር ገቢ መደረግ አለበት፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራቾች ሃሳቡን ማለትም የፋይናንሽል ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰዴ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት እና 31 ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እንዲሁም ኮፒ ማስገባት አለባቸው፡፡ በመሆኑም ኮፒ ባለማስገባቱ ከውድድር ውጭ ሊያስደርግ አይችልም፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 ጋዜጣው በወጣ በ31 ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይክፈታል፡፡ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን መክፈት መብት አለው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 555 41 73 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የሰዴ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here