ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
86

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለ4ቱም ፑል መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 ጽ/መሳሪያ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃ ፣ሎት 3 ቋሚ አላቂ ፣ሎት 4 ፖሊቲን ቲዩብ እና ሎት 5 ኮድ LN-166 የመኪና እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. እቃው ወይም የአገልግሎት ግዥ መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነዶች ግልጽና የሚነበቡ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለየአንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 ጽ/መሳሪያ 17,000.00 ፣ሎት 2 የጽዳት እቃ 3,000.00 ፣ሎት 3 ቋሚ አላቂ 4,000.00 ፣ሎት 4 ፖሊቲን ቲዩብ ብር 3000.00 ፣ሎት 5 ኮድ 166 የመኪና እቃ 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ /ቢድ ቦንድ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ05/52017 እስከ 19/05/2017 11.30 ደረስ ጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በ20/05/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የአንድ ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ከሆነ ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየው በሎት (በድምር ዋጋ ነው)፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  10. ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃጸር የተጋነነ ከሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
  11. ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍል አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል የማይችል ሲሆን በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ ማሻሻል አይችልም፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here