ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
149

የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. ጎርደማ ቁጥር 2፣ዱዱ ቁጥር 2፣ ጨረጨራ ቁጥር 10 የኦፕተር ቤት፣ጥበቃ ቤት፣ ሻወር እና ሽንት ቤት የግንባታ ስራ ለማሰራት ፣ሎት2. የመሬት ቁፋሮ እና አፈር መመለስ እና የግንባታ ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ቦታዎችም ጎርደማ ፣ ዱዱ ቀበሌ 14 ፤ ጨረጨራ ቀበሌ 11 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ /የታደሰ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2.  የግዥው መጠን ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሽህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናሉን ኮፒውን እና ሲፒኦ በተለያዩ ፖስታ ታሸጎ አጠቃሎ በአንድ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. ጨረታው  ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡
  8. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ /ጽ/ ቤት በተጠቀሱት የውሃ መገኛ ቦታዎች አገልግሎቱን በመስጠት ግንባታውን መገንባት የመሬት ቁፋሮ እና አፈር መመለስ እንዲሁም የግንባታ ስራዎች መሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 320 5079 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ አድራሻ ባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 08 ከዊዝደም ወደ ፖሊ መሄጃ አማራ ባንክ የተከራየበት ህንጻ ነው፡፡

የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here