የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የከብትና የበግ ስጋ፣ ሎት 2 እንቁላል፣ ሎት 3 አትክልትና ፍራፍሬ፣ ሎት 4 ጤፍ፣ ሎት 5 የታሸገ የማዕድን ውሃ፣ ሎት 6 ዳቦ፣ ሎት 7 ኬክና ቆሎ፣ ሎት 8 የባልትና ውጤቶች፣ ሎት 9 የወፍጮ አገልግሎት፣ ሎት 10 ሸቀጣሸቀጥ፣ ሎት 11 በርበሬ፣ ሎት 12 ማገዶ እንጨት እና ሎት 13 ቅመማቅመም እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ውል ተይዞ የሚቀርብ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በየሎቱ በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያ በጋዜጣ /በኦላይን/ ከወጣበት ከግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዩቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከግንቦት 19/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 04/2016 ዓ.ም 4፡ዐዐ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ሰኔ 04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በሥራ አመራር ኢንስቲትዩት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡