ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
91

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ስልጠና ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ ሰነዱ መሠረት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. አግባብነት ያለው ህጋዊና በዘርፉ የተሰማሩ ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 01 በመክፈል የጨረታ ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ግዥው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ከፖስታው ላይ በመጻፍ ቢሮ ቁጥር G001 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ስትወዳደሩ የምታቀርቡትና ዋጋ የምትሞሉት በኦርጅናል ብቻ መሆኑን ማወቅ ይጠበቅባችኋል፡፡ ቴክኒካል የሚያስፈልግ ስለሆነ ቴክኒካልና ፋይናንሻል በሚል ሁለት ፖስታዎች ማስገባት አለባችሁ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው የገቢ ደረሰኝ በማሰቆረጥ እና ማስረጃዉን ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
  9. ጨረታዉ ከተከፈተ በኃላ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተሞላን ዋጋ ማሻሻል መለወጥ ወይም ጨረታዉን ሰርዣለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ማለትም 27/05/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው ስራና ስልጠና ቢሮ ቁጥር G001 ውስጥ ይከፈታል፡፡ አስራ ስድስተኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ውድድሩ በተናጠል መሆኑን አውቃችሁ መሙላት ይኖርባችኋል፡፡
  12. ቢሮዉ ጨረታዉን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ /መረጃ/ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 53 97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብክመ ስራና ስራና ስልጠና ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here