የስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለፍርድ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት 2 ህትመት እና ሎት 3 ፈርኒቸር የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በእያንዳንዱ ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆንና ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችና አገልግሎቶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ከላይ ለተጠቀሱት የአገልግሎት00 /ሃያ ብር/ በመክፈል ስ/ወ/ፍ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጥሬ ገንዘብ በዋና ገንዘብ ያዥ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በማስያዝ የስያዙበትን ኮፒ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ ዋስትና አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 09 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ስዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖረባቸዋል፡፡
- በጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ/ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/ አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 09 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 09 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 64 66 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ርክክቡ የሚፈጸምበት ቦታ በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ፍ/ቤቱ በአንድ ሰነድ/ የተዘረዘሩትን ተመሳሳይ እቃዎች ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡
- ፍ/ቤቱ በአንድ ሰነድ በአንድ ምድብ /ሎት/ የተዘረዘሩትን ተመሳሳይ እቃዎች ተጫራቹ በሞላው ዋጋ የጨረታ ሰነድ አሸናፊው የሚለየው በጠቅል ዋጋ ነው፡፡
የስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት