ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

የቆቦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2017 ዓ.ም  በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃ ፣ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት 4 ፈርኒቸር ፣ሎት 5 የደንብ ልብስ ፣ሎት 6 ህትመት ሎት 7 የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛዉም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. በሥራ ዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ /ቲን/ ያላቸዉ እና የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከላይ ከሎት 1-7 የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ተጫራቾች ጨረታዉን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ስለሚቆይ ቆቦ ሆስፒታል ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 94 ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 የሚታሸግና በዚሁ ቀን 4፡00 ላይ ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. ተወዳዳሪዎች የምትጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በታሸገ ፖስታ ዋናዉንና ኮፒዉን በተዘጋጅዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 12/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የሚወስዱ ሲሆን ዉድድሩ በሎት /በጠቅላላ ድምር/ ስለሚሆነ የተሰጣችሁን የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ መሙላት ይኖርባችኋል፡፡ ነገር ግን የጨረታ ሰነድ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይደረጋል፡፡
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ዝርዝር ስማቸዉን ፣ፊርማቸዉን እና አድራሻቸዉን በህጋዊ ማህተም መርገጥ በቻል አለባቸዉ፡፡
  8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜዉ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታዉ እራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን በማባዛት ወይም በኮፒ ሞልቶ ለመወዳደር የሚሞክር ተጫራች ከጨረታ ዉጭ ይሆናል፡፡ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ሳይመለስ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  10. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን እቃ በራሳቸዉ ወጪ ከተቋማችን ድረስ በማምጣት ገቢ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ በግዥ ሂደቱ ላይ ሃያ በመቶ ከፍና ዝቅ ብሎ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ተጫራቾች ማጭበርበር ሙስና ወይም ጉቦ መስጠትን እና መቀበል ሳይኖርበት በሃገሪቱ ህጎች ላይ የተደነገገዉን ህግ የሚያከብሩ መሆን አለባቸው፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 34 04 95 ወይም 09 21 04 95 18 ደዉለዉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቆቦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here