ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
94

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የጣና ክፍለ ከተማ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን የ2017 በጀት ዓመት የጽህፈት ፣የጽዳትና አላቂ ቋሚ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የጽህፈትና የጽዳት አላቂ ቋሚ እቃ ግዥ መጠኑ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከኦርጅናል ጋር በማመሳከር ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የጽህፈት ፣የጽዳትና አላቂ ቋሚ እቃዎች ግዥውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጽህፈት፤ የጽዳት አላቂ ቋሚ እቃዎች   ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን ጣ/ክ/ከ/ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መዉሰድ ትችላላችሁ፡፡
  9. ይህ መመዘኛ የምታሟሉና መወደደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከቀን 12/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀን በአየር ላይ በመዋል በ15 ተኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡00 ጨረታዉ ተዘግቶ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 በጣና ክፍለ ከተማ የግዥ ፋይናንስ ቢሮ ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ዓይነት በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም በዋናና ኮፒ  በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  1. አሸናፊ የሚለየዉ በሎት ድምር ነዉ፡፡
  2. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  3. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጣ/ክ/ከ/አስ/ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 84 በመደወል ዝርዝር ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጣና ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here