የአዊ/ብሔ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ለ2007 በጀት ዓመት ለአዊ/ብሄ/አስ/ ውሃ እና ኢነርጅ ልማት መምሪያ ለመጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዛው የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ስለሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን እና የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ መሂ 1 ግቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ከ12/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 በማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የማወዳደሪያ ሥርዓቱ በጥቅል ዋጋ ነው፡፡
- የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በግ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ከ12/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/05/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዊ ብሄ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ግን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፣ ነገር ግን 16ኛው ቀን (የሚከፈትበት ቀን) ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጅ የሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር /ታክስ/ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ወጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 227 00 66 ወይም 09 18 06 37 94 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዊ/ብሔ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ