የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በብ/የሚ/የግ/ግክ/ ቡድን በ2017 በጀት አመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የማንጎ ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የብቃት ማረጋገጫ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የግዥ መጠን ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የማንጎ ዘሩ 50 (ሃምሳ) ኩንታል ሁኖ በዛፉ ላይ በጣም የበሰለ ወደ ቢጫነት የተቀየረ ከበሽታና ተባይ ነጻ የሆነ ያልተላጠ እና ግብዓቱ ሲቀርብ ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ የአሰሪው መ/ቤት እና የተጫራቹ ሙሉ ስም አድራሻ ፊርማ ማህተም በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት00 /ሰላሳ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ከቢ/ወ/ገ/ኢ/ል/ፅ/ቤትደ/ሂ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢ/ወ/ግ/ፅ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ12/05/2017 ዓ.ም እስከ 30/05/2017 ዓ.ም 10፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን 10፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታዉን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግብ/ፅ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን በቢሮ 06 በ01/06/2017 ዓ.ም በ 3፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ሃያ በመቶ የመጨመርም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሚከፍትበት ቀን ብሄራዊ በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ግብዓቱ የሚቀርበው በሙሉ ወይን ዉሃ ችግኝ ጣቢያ ሲሆን በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ሰለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 06 04 ወይም 09 13 79 98 34 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት