በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሎት1. የኮሌጁ አጥር የእጅ ዋጋ እና ቁሳቁስን ጨምሮ /ጥቅልዋጋ/ በማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቲን /ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርትፊኬት ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በከተማ ልማት የግንባታ ምስክር ወረቀት ከደረጃ 7 እና በላይ ያላችሁ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸውጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር00 /ሁለት መቶ / ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድቦንድ/ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከኮሌጁ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጠ/ጤ/ሣ/ኮሌጅ በግዥና /ፋ/ን/አስ/ ቡድን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀን እስከቀኑ 10፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ስዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚህ ዕለት ከቀኑ 10፡30 ታሽጎ በ22ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- የስራዉ ዝርዝር/ሰፔስፊኬሸን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ዉድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡በጨረታው ላይ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 058-448-0234 ደውለው መጠየቅ ወይም ጠዳ ጤና ሳ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ