የጨረታ ቁጥር፡-006/2016
የአብክመ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛ እና ከተለያዩ ፕሮግራሞች በተገኘ በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የውሃ ማጣሪያ ቦትል፣ ሎት2. የውሃ ማከሚያ ኬሚካሎች፣ ሎት3. የቢሮ ስም ያለበት ሪሊፍ፣ ሎት4. የሦስተኛ ወገን የመድን ሽፋን ዓመታዊ ውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ሎት፣ ሎት02. እና ሎት04. ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዳቸው 40,000.00 /አርባ ሽህ ብር/ ለሎት 03. 10,000.00 /አስር ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመውሃና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ 00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ሕጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀንከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ይከፈታል ፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 013 2/ 058 220 10 87 ዘወትር በሥራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቀበሌ 07 ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት