የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት የሚያስፈልጉ ሎት1.የሰራተኞች የደንብ ልብስ /ብትን ጨርቆች/፣የተዘጋጁ ሸሚዞች፣ የወንድና የሴት ቆዳ ጫማ፣ የወንድ የፕላስቲክ ቦት ጫማ እና ልዩ ልዩ አልባሳት ፣ ሎት2.የፅዳትና ጽህፈት መሳሪያዎች፣ሎት3. የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት4. የHDPE መገጣጠሚያና የቧንቧ መገጣጠሚያ የብረት ፣ሎት5.ቱልስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ፣የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢዎች የተመዘገቡ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን የዕቃዎች የጠቀሜታ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ናሙና ወይም ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምፕል ወይም የምርት መግለጫ ካታሎግ በቴክኒካል ፖስታ ውስጥ አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰአት ቢ.ቁ 03 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል በማለት ህጋዊ መረጃዎችን በቴክኒካል ፖስታ ውስጥ በማድረግ እንዲሁም ፋይናንሽያል መረጃዎቻቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በፋይናንሸያል ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ከጧቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 01 በይፋ ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የዕረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታ ሰነዱ እስከ 4፡00 ድረስ በማስገባት ከቀኑ 4፡30 በይፋ ይከፈታል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ስ.ቁ 033-551-02-72 በመደወል ወይም በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት