ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
82

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የባህል ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም የቅርስ ጥ/ል/ፈ/ጽ/ቤት የጽ/መሳሪያ ፣የጽዳት ዕቃ ፣የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣ፈርኒቸር ፣የመኪና ጎማ ከነ ካላማዳሪው እና የመኪና መለዋወጫ ስፔርፓርት ዓመታዊ ግዥ ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የ2017 በጀት ዓመታዊ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆንናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ተነባቢና ግልጽ የሆነ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን00 /ሁለት መቶ ብር/ ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Unconditional Bank Garntee/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሪት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ /ዳይሬክቶሪት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 42 70 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 58 64 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ ባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 16 ግብርና ምርምር ቢሮ ፊት ለፊት ካለው ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 እንገኛለን፡፡

የአብክመ ሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here