ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አማካኝነት ለምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከአ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባባሪያ ኮሚሽን በተገኘው የበጀት ድጋፍ በድርማ ወንዝ ፣የመገጭ ወንዝ ፣ሱዳን ገደል ወይም አምባገነን ወንዝ የጎርፍ መከላከል ሥራ እንዲሰራላቸው በቁጥር ግ/ል/339/1/6 በቀን 07/05/2017 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ በጠየቁት መሰረት የእስካቫተር ማሽን ተከራይቶ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. የዘመኑን የ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
  3. ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከ19/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ምስራቅ ደምቢያ ወረዳ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የምንከራየው እስካቫተር ማሽን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየዉ  በሎት ድምር በቀረበዉ ዝቅተኛ ዋጋ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 19-05/2017 ዓ.ም እስከ 03/06/2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኝት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም  በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ  የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 04/06/2017 ዓ.ም በ3፡30   ታሽጎ በግዥ ፣ፋይናንስ  ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን 04/06/2017 ዓ.ም በ00 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ  የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
  11. የኤክስካቫተሩ ዓይነት ባለሰንሰለት መሆን አለበት እንዲሁም አሸናፊው 3 እና ከዚያ በላይ የእስካቫተር ማሽን አቅርቦ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ እንዲሁም፡- የሎቤድ ኪራይ ቦታው ድረስ ማለትም በድርማ ወንዝ ፣የመገጭ ወንዝ፣ ሱዳን ገደል ወይም አምባገነን ወንዝ በየቀበሌያቸዉ ድርስ አዘዋዉሮ መስራት  የሚችል ሆኖ የመወሰጃና የመመለሻ በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ዋጋው የሚሞላው ነዳጅን ጨምሮ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ወይም ነዳጅ በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈን  ይሆናል፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራች ሶስት እስካቫተር እና ከዚያ በላይ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
  13. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ማንኛዉም ተጫራቾች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ዉስጥ የአሸነፉበትን የማሽን ኪራይ ወይም አገልግሎት  በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አማካኝነት እስከ ሥራ ቦታው ማሽኑን በማቅረብ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  15. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 ወይም 09 18 73 90 06 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም

የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here