የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የሚፈልጋቸውን ሎት 1 ፕላስቲክ የውኃ ማስተላለፊያ ቱቦ (HDPE Pipes) ፣ሎት 2 የብየዳ ጀኔሬተር (ዌልዲንግ ጀኔራር) ፣ሎት 3 የደንብ ልብስ እና ሎት 4 የውኃ ማጣሪያ ኬሚካል (ኮፐር ሳልፌት) በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ በጨረታዉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /ቫት/ የሆኑ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ህጋዊ /ሲፒኦ/ ብቻ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጎ/ከ/ው/ፍ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 27 በመግዛት በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ከቀን 21/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 05/06/2017 ዓ.ም ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 14 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ተለያይቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል /ቴክኒካልና ፋይናንሻል እና አንድ ኮፒ/ ቴክኒካልና ፋይናንሻል/ የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከቀን 21/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀን 05/06/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ በቀን 05/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ በአገር አቀፍ በዓል ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 የሥራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የሥራ ቀን ይቆጠራል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 211 33 16 /058 112 06 97 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ፡፡
የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት